አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፦ የሕዝቡን ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኝ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።
አቶ አደም ፋራህ የብልጽግና ፓርቲ እሳቤዎች መሰረት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ የህዝብን ጥቅም በዘላቂነት ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ከእነዚህ የልማት ስራዎች መካከል በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን መንደርንና ቤተሰብን ማዕከል በማድረግ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር እንደሚገኝበት ለአብነት ጠቅሰዋል።
መርሃ ግብሩን ከወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ ስራዎች ማከናወን መቻሉንም አመልክተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025