አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- የስራ ዕድል ፈጠራ አማራጮችን በማስፋት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።
አለምአቀፉን የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በሴቶች የተመረቱ ምርቶች ባዛርና ኤግዚቢሽን፣ የምርት ማሳያ ጋለሪዎች እንዲሁም የነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ላይ ጉብኝት ተደርጓል።
ጉብኝቱን ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይንሸት ዘሪሁንን፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ አገራት ሴት አምባሳደሮች ናቸው።
የአዲስ አበባ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይንሸት ዘሪሁን መንግስት ባለፉት ዓመታት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል።
በዚህም ሴቶች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መጥቷል ነው ያሉት።
ቢሮው የተለያዩ የስራ ዕድል ፈጠራ አማራጮችን በማስፋት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
በሴቶች ብቻ የተመረቱ የተለያዩ ምርቶችም የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን በመጥቀስ።
ቢሮው በቀጣይም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አረጋግጠዋል።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ''ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል'' በሚል መሪ ሀሳብ በዓለም ደረጃ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025