ደሴ የካቲት 30/2017 (ኢዜአ)- በአማራ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት 8 ሺህ 929 ኪሎ ሜትር የነባር መንገድ ጥገናና የአዲስ መንገድ ግንባታ ማከናወን መቻሉን የክልሉ መንገድ ቢሮ አስታወቀ ።ፎቶ አለው
ቢሮው የ2017 ዓ.ም የሰባት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በደሴ ከተማ እያካሄደ ነው።
የቢሮው ኃላፊው ጋሻው አወቀ(ዶ/ር) በመድረኩ እንደገለፁት በክልሉ ነባር መንገዶችን በመጠገንና አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው።
ይህም የመንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት በማሳለጥ እንዲሁም የህብረተሰቡን መስተጋብር ለማፋጠን የሚያስችል ስራ መሰራቱን አስረድተዋል።
በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከተከናወነው 8 ሺህ 929 ኪሎ ሜትር ውስጥም 8 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የነባር መንገዶች ጥገና ሲሆን፤ ቀሪው 329 ኪሎ ሜትር ደግሞ የአዲስ መንገድ ግንባታ ነው ብለዋል።
በአዲስ የመንገድ ግንባታና በነባር መንገዶች ጥገና ስራው ላይም ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበቱና በቁሳቁስ እያደረገ ያለው ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ምመጣቱን ተናግረዋል።
ይህም ቢሮው ክረምቱ ከመግባቱ በፊት በቀሪ ወራት በሁሉም ዘርፎች የታሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የያዘውን ግብ ለማሳካት እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት አስገንዝበዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን በበኩላቸው በዞኑ የመንገድ ተደራሽነቱን በማሳደግና በአገልግሎት ብዛት የተበላሹትን በመጠገን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዚህም ባለፉት ወራት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ የተቻለ ቢሆንም ከህብረተሰቡ የመልማት ፍላጎት አንጻር ሲታይ በቀጣይ ወራት የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
በመድረኩ የክልል፣ የዞን፣ የከተማ አመራር አባላትን ጨምሮ አጋርና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025