የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ከ78 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካፒታል የተመደበለት ባለ ብዙ ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ እንዲከናወን ተወሰነ

Mar 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2017(ኢዜአ)፦ ከ78 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካፒታል የተመደበለት ባለ ብዙ ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ እንዲከናወን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ውሳኔ አሳለፈ።

ቦርዱ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን ከውሳኔዎቹ መካከል በአንድ ባለሀብት ባለ ብዙ ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት የቀረበው ጥያቄ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ ያሳለፈው ውዳኔ ይገኝበታል።


በጥያቄው ላይ ቦርዱ በስፋት ከተወያየ በኋላ ባለ ብዙ ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሆኖ እንዲሰየም እና ጥያቄ አቅራቢዎቹም በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ውሳኔ ማሳለፉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አሰያየም፣ የመሬት አመዳደብ እና አጠቃቀም መመርያን ጨምሮ በቀረቡለት ሌሎች ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔ መስጠቱም ተመላክቷል።

ቦርዱ በሀገሪቱ ምቹ እና ሳቢ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት እእነዲሁም ለኮሚሽኑ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጹም በመረጃው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.