
ባሕር ዳር፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፡- በባሕር ዳር የከተማ ግብርና ከ4 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ እየለማ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የግብሮና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የሆልቲካልቸር ባለሙያ ሞላልኝ መንግስቱ፤ በአስተዳደሩ የከተማ ግብርናን በማስፋፋት በምግብ ራስን ለመቻል የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም አሁን ላይ 4 ሺህ 893 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ እየለማ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህም 299 ሺህ ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል።
ከዚህም 3 ሺህ 200 ሄክታር የሚሆነው በስንዴ ሰብል የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመው፤ ከ136 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል።
በከተማ የግብርና ልማት በምግብ ራስን ለመቻልና የተሻለ አመጋገብ እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን ነው ባለሙያው ያስረዱት።

በዘርፉ ልማት ከተሰማሩ ወጣቶች መካከል ልሳነወርቅ ሰይፉ በሰጠው አስተያየት፤ በርካታ ወጣቶች በከተማ ግብርና የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግሯል።
በማህበር ተደራጅተው ከሚያከናውኑት የአትክልት ልማት በተያዘው ዓመት እስከ 100 ሺህ ብር ለማግኘት አቅደዋል።

በማህበሩ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራው ወጣት ግዛት ክፍሌ፤ በዘርፉ ልማት ለበርካቶቻችን የስራ እድል ተፈጥሮልን ተጠቃሚ ሆነናል ብሏል።
ከዚህ በሚያገኘው ገቢ በመቆጠብ በቀጣይ የራሱን ቋሚ ስራ ለመጀመር እቅድ ያለው መሆኑንም ተናግሯል።
በከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት ከተካሄደው የበጋ መስኖ ልማት ከ230 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱ ታውቋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026