አዲስ አበባ ፤መጋቢት 6/2017(ኢዜአ)፦በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ የግዥ ስርዓትና የፕሮጀክቶች አፈፃፀም መጓተት አፋጣኝ መፍትሔ የሚሹ መሆናቸውን የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።
የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሚያደርጉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ መሆኑን አመላክቷል።
የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ኮሚሽን በትምህርት ዘርፍ የሙስና ሥጋት ተጋላጭነት ዙሪያ ባደረገው ጥናት ላይ ከተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው የግዥ፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም መዘግየት፣ የመምህራን በተደጋጋሚ በክፍል አለመገኘትና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ጉዳዮች ላይ የሙስና ተጋላጭነት መኖሩ በጥናቱ መለየቱን ገልጸዋል።
ህገወጥ ቅጥር፣ ዝውውርና የደረጃ እድገት፣ የክትትልና የድጋፍ ስርዓት አለመገንባትን ጨምሮ የአሰራር ግልፅነት መጓደል መኖሩን የጥናቱ ግኝት ያሳያል ብለዋል።
የጥናት ግኝቱ በሶስት ደረጃዎች መለየቱን ተናግረው በዚሁ መሰረት ለችግሩ ከአፋጣኝ ጀምሮ ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባም ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ፤ በዘርፉ የተለዩ የሙስና ተጋላጭነት እና ለብልሹ አሰራር የሚዳርጉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ይዘረጋል ብለዋል።
ከዚህም ባሻገር ተጠያቂነትን የማረጋገጥና የሙስና መከላከል አቅምን የማሳደግ ስራ በስፋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በበኩላቸው በጥናት ለተለዩ ስጋቶች የሚመለከታቸው ተቋማት ዘላቂ የመፍትሔ እርምጃ እንደሚወስዱ አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025