አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፦የአፋርና የሶማሌ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሰመራ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ ኢድሪስን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።
ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ በጉብኝታቸው በሰመራ ከተማ እየተገነባ የሚገኝ የዳቦ ፋብሪካ እንዲሁም የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችንና የከተማው የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።
ትናንት ምሽት የአፋርና የሶማሌ ህዝቦችን አብሮነትና ትስስር ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ የጋራ ኢፍጣር መርሃ ግብር በሰመራ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025