አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በልማት መስክ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር በማስፋት ያላቸውን አጋርነት ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱኔ ክሮግስትሮፕ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ዴንማርክ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ጨምሮ ያላት የልማት ትብብር ከኢትዮጵያ የቅድሚያ የትኩረት መስኮች ጋር የተናበቡ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ የመጣውን የልማት እርዳታ ፈተና ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ ፕሮግራሞችን በጋራ ፋይናንስ ማድረግ እና የረጅም ጊዜ ዘለቄታቸውን ማረጋገጥ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የመንግስትን የፋይናንስ ግልጸኝነት ከማረጋገጥ ጥረቶች ጋር ተዳምሮ በተለያዩ ዘርፎች ለውጦች እንዲመጣ ማድረጉን አመልክተዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ጉምሩክ እና የታክስ አስተዳደር ለውጥ ከመጠባቸው ዘርፎች መካከል ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱኔ ክሮግስትሮፕ የዴንማርክ የልማት ፕሮግራሞች ከኢትዮጵያ ፍላጎቶች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ዴንማርክ በቀጣይ ለኢትዮጵያ በዘላቂ ልማት ላይ ያተኮረ ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቁመዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ ያላቸውን ጠንካራ እና ፍሬያማ አጋርነት ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ዴንማርክ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የምታደርገውን አዲስ የልማት ፕሮግራም እ.አ.አ ጁን ወር 2025 ላይ እንደምታፀድቅ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025