ጋምቤላ፤መጋቢት 10/2017 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ አስገነዘቡ።
በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላትና የዘርፉ ባለድርሻዎች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ዛሬ ማምሻውን በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሯ፥በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት እያደረጉ ነው።
ችግሮቹን ለመፍታት የዘርፉ አመራር አካላትና ባለድርሻዎች በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ለችግሩ አስተዋፆ ባላቸው አካላት ላይ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሯ፥ በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ተከታትሎ እርምት የሚወስድ ግብረ ሃይል እንዲቋቋምና በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላትና የዘርፉ ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025