
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ)፦ የሸማቹን መብት ለማስጠበቅ ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በተጨማሪ መብት ጥሰው በተገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ ጊዜ የሚከበረው የሸማቾች ቀን በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ተከብሯል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሊቁ በነበሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የሸማቹ መብት በተለያየ መንገድ የሚጣስበት ሁኔታ አለ፡፡
ሸማቹ መብቱን እንዲያውቅ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተከታታይ ዓመታት በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡
በዚህ ዓመት ብቻ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የሸማቾች መብትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱን ለአብነት አንስተዋል፡፡
የሸማቹን መብት የሚጥሱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ አንስተው በበጀት አመቱ ሰባት ወራት ብቻ ከ 109ሺ በላይ ነጋዴዎች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፤ የሸማቾች መብት እንዲጠበቅ ከማድረግ አኳያ በከተማ አስተዳደሩ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።
ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው ምርት እንዲያገኝ እንዲሁም ጊዜ ካለፈባቸው ምርቶች እንዲጠበቅ የማድረግ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
ይህም ቢሆን ግን ከችግሩ አኳያ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን አንስተው፤ በቀጣይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ሌሎች ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር ፕሬዚዳንት ፈታኑር አህመድ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ለሸማቹ ግንዛቤ ከማስጨበጥ በተጨማሪ መብቱን የማያከብሩ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው፡፡
አምቦ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ለንብ ማነብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ...
Jun 14, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርስ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የክልሉ ምክት...
Jun 11, 2026
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨ...
Jun 1, 2026
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ደግፎ የማብቃት ሥራው ተጠናክሮ እ...
May 26, 2026