አሶሳ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ):-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከበጋ መስኖ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥በክልሉ ዘንድሮ በበጋ መስኖ 59 ሺህ ሄክታር ማሳን በማልማት 13 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
የመስኖ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግ የባለሙያ እገዛና 30 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ጥረት መደረጉን አክለዋል።
እስካሁን ከለማው መሬት 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል አርሶአደሩ የዝናብ ወቅትን በመጠበቅ ብቻ የሚያመርትበትን አሰራር በመቀየር በበጋ መስኖ ልማት ከሁለት ጊዜ በላይ በማልማት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
አርሶ አደሩ በበጋ መስኖ ሽንኩርት፣ቲማቲም ፣ድንች፣ ጎመንና ሌሎችንም የአትክልት ዓይነቶች በስፋት በማምረት ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በክልሉ ካሉ ትልልቅ ወንዞች ውሃ በመሳብና ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከአርሶአደሩ በተጨማሪ ባለሃብቶች በበጋ መስኖ መሰማራታቸውን አቶ ባበክር ተናግረዋል።
ይህም የአርሶ አደሩን የስራ ባህል የቀየረ እና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘንድሮ በበጋ መስኖ ለማልማት የታቀደውን ለማሳካት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተመልክቷል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025