የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ድጋፉን ይቀጥላል

Mar 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ):- የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።

በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር እና በሮም መቀመጫቸውን ያደረጉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ቋሚ ተጠሪ ደሚቱ ሃምቢሳ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ረዳት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፋይናንስ ኦፕሬሽን ዲፓርትመንት ኃላፊ ሀርናን ዳነሪ አልቫራዶ ጋር ዛሬ በሮም ተወያይተዋል።

አምባሳደር ደሚቱ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ የመስኖ ልማት እና ሌሎች የግብርና ዘርፎች ውጤታማ ስራ ማከናወኗን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ረዳት ምክትል ፕሬዝዳንት ሀርናን ዳነሪ አልቫራዶ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችው ውጤት የሚደነቅ እና ለአፍሪካ እና ሌሎች ዓለም አገራት እንደ ተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል።

የልማት ፈንዱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ አገራት በአነስተኛ ማሳ ይዞታ ላይ ተመሰርተው የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድግ እና የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም ግብርና ለመገንባት እያደረጉ ያለውን ጥረት የሚደግፍ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.