አዲስ አበባ ፤መጋቢት 18/2017 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል በሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ውጤታማና ተደራሽነትን ማድረግ መቻሉን የክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም በሰጡት መግለጫ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ማሳደግ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ውጤታማና ተደራሽ የማድረግ ስራዎች በትኩረት እየተሰራባቸው ነው ብለዋል።
በተለይ ከለውጡ በፊት የነበሩ አሳሪ ህጎችን በማሻሻልና ለዘርፉ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ፖሊሲዎችን በማውጣት ዘርፉን የማዘመንና ከጊዜው ጋር መራመድ የሚያስችል አሰራር መገንባት መቻሉንም አመልክተዋል።
በዚህም የመንግስት ተቋማት የደንበኞችና የተቋማት የመረጃ (ሰነድ) አያያዝን በዲጂታል በመቀየር ደህንነቱ የተጠበቀ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እገዛ ማድረጉንም ነው የተናገሩት።
የመንግስት አገልግሎት መስጫዎችን ወደ አንድ ቋት በማስገባት ሀሰተኛ ሰነድ እና የመረጃ ማጭበርበር ችግሮችን ለመከላከል መቻሉን አስረድተዋል።
በቀጣይም መንግስት ሊገነባው ላቀደው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዘመን በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ጀማል መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025