አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2017(ኢዜአ)፡- አዲስ አበባ በማያቋርጥ የለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ወደ አገልግሎት የገቡት 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቢሶች ጠዋትና ማታ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ያለውን የትራንስፖርት ሰልፍ እና የህዝብ እንግልት የሚቀንሱ ናቸው ብለዋል።
መንግስት ያወጣውን የአየር ብክለት የመከላከል ፖሊሲን በተሟላ ሁኔታ መተግበር ብሎም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገባውን ነዳጅና የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ የሚረዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኤሌክትሪክ አውቶቢሶቹ የዲጂታል የትኬት ስርዓትን ተግባራዊ የሚያደርጉ፣ ዲጅታል ባስ ካርድ ሥርዓት (Bus Card System) እውን የሚያደርጉ፣ በካሜራ እና ጂፒኤስ ድጋፍ እና ቁጥጥር የሚደረግባቸው እንዲሁም ሃገር ውስጥ የበለፀገ ሲስተም እንደተገጠመላቸው አመልክተዋል።
የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሳለጥ እና ጥራትና ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለህዝብ ለመስጠት ከለውጥ በፊት የነበረውን የአውቶቢስ ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን ጠቁመዋል።
ከለውጡ በፊት ከ20 በመቶ በታች የነበረውን የመንገድ ሽፋን በ10 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉንም አስረድተዋል።
ተርሚናሎችን እና የመኪና ማቆሚያዎችን በ10 እጥፍ ማሳደግ የቻልንበት መሰረታዊ ለውጥ መጋቢት 24 የተጀመረው ለውጥ ያመጣው መሰረታዊ ውጤት ነው ብለዋል ከንቲባዋ።
ዛሬ የግል ኦፕሬተር ወደ ስራ መግባቱ በአሰራር እና በአገልግሎት ላይ አዳዲስ አሰራሮችን ወደ ስራ በማስገባት የበለጠ ህዝቡን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ያለንን ቁርጠኝነት ያሳየንበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025