ባህር ዳር፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚውል 68 ሚሊዮን ብር ከማህበረሰቡ ማሰባሰብ መቻሉን የክልሉ የህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መጋቢት 11/2017ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከሰጡት ማብራሪያ ወስጥ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ይገኝበታል።
በዚሁ ማብራሪያቸው እየተገባደደ የሚገኘውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በጋራ ሪቫን በመቁረጥ ታሪክ እናደርገዋለን፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ መቻልን ያሳየችበት ነው ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠ ጊዜ አንስቶ የአማራ ክልል ሕዝብ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ድጋፉን በሁሉንተናዊነት ሲያደረግ ቆይቷል፤ አሁንም ቀጥሏል።
የክልሉ የህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አባይነህ ጌጡ፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለፍፃሜ ለማብቃት በሚደረገው ጥረት የክልሉ ህዝብ አሁንም የጎላ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ለኢትዮጰያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል።
ለዚህም በዚህ በጀት ዓመት 100 ሚሊዮን ብር በቦንድ ሽያጭና ልገሳ ለማሰባሰብ ታቀዶ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው፤ ከዚህም ባለፉት ስምንት ወራት 68 ሚሊዮን ብር ያህሉን መሳካት እንደተቻለ አስታውቀዋል።
የተሰበሰበው ሃብትም ባለፈው መሉ የበጀት ዓመት ከተሰበሰበው ጋር ሲነጻጻር ከእጥፍ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።
ለዚህም ህብረተሰቡ አሁንም ለሀገራዊ ፕሮጀክቶች ፍፃሜ መድረስ በጉጉትና በታላቅ ተነሳሽነት እያገዘ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በዚህ ዓመት በተከናወነው ስራ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች የላቀ ሚና መወጣታቸውን ጠቅሰው፤ የመንግስት ሰራተኛው፣ ነጋዴውና አርሶ አደሩም አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ አመላክተዋል።
በቀሪ ወራትም ዕቅዱን በተሟላ መንገድ ለማሳካት በተቀናጀ መንገድ በንቅናቄ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ህብረተሰቡም ለግድቡ ግንባታ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ይበልጥ እንዲያጠናክር መልዕክት አስተላልፈዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠ ጊዜ አንስቶ የክልሉ ሕዝብ በጥሬ ገንዝብ ከ1 ነጥብ 32 ቢሊዮን ብር በላይ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስታውሰዋል።
እንዲሁም የህዳሴ ግድቡን ከደለል ለመከላከል በተከናወነ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራም ከ38 ቢሊዮን ብር በላይ የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከት እንደተቻለ ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025