ወልዲያ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የሚገነባው የ16 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ እየተፋጠነ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ።
በከተማ አስተዳደሩ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሃመድ-ሷሊህ ያሲን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማት ስራው ከተማዋን ማዘመን የሚያስችል ነው።
የኮሪደር ልማቱ ከጀነቶ በር - ሸህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ አደባባይ-ስታዲየም- እቴጌ መናፈሻ- ከአዳጎ አደባባይ- ጎንደር በር አድርጎ በፒያሳ እስከ ጉቦ በር የ16 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑን ተናግረዋል።
በ117 ሚሊዮን ብር በጀት የሚገነባው ከአዳጎ አደባባይ - ሙጋድ እስከ ጎንደር በር አደባባይ ያለው የ1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ያለውን የኮሪደር ልማት ዘንድሮ ለማጠናቀቅ ስራው እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ የኮሪደር ልማትም ለ200 ሰዎች አዲስ የስራ እድል የፈጠረላቸው መሆኑን ጠቁመው፤ መላው የከተማው ህዝብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጠል መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ከወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች መካከለ አቶ ፍስሃ አያሌው በሰጡት አስተያየት፤ ተወልደው ያደጉባት ጥንታዊት የወልዲያ ከተማ በኮሪደር ልማቱ ገጽታዋ እየተቀየረ መምጣቱን ገልጸዋል።
በከተማዋ ባለው ጠባብ መንገድ እሰከ ዛሬ ተሽከርካሪዎችና እግረኞች በመጋፋት ለአደጋ እየተገለጥን ነበር ያሉት ነዋሪው፤ አሁን ላይ እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ይሄን መሰረታዊ ችግር የሚፈታ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የስራ እድል አግኝተንበት ቤተሰባችንን እየመራን ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025