Apr 3, 2025
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ፋርማሲዩታካል ዘርፍ መሰማራት ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካን የገበያ ድርሻ ማግኘት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮ ህንድ የፋርማሲዩቲካል የንግድና የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በፎረሙ ላይ ከ80 በላይ የህንድ መድኃኒት፣ የህክምና ግብዓትና ቁሳቁስ አምራች ድርጅቶች ተሳትፈዋል።
ኮሚሽነሩ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎቷን የምታሟላው ከወጪ በማስገባት እንደሆነ ገልጸው በ10 ዓመት ሀገራዊ የልማት እቅዱ ይህንን ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ግብ መደረጉን ጠቁመዋል።
ለዚህም የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዘመናዊ መሰረተ ልማትን አካቶ መዘጋጀቱን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ለሚሳተፉ ባለሀብቶች የተለያዩ የታክስ ነጻና ማበረታቻዎች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል።
የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል የኢንቨስትመንት መስክ ባሉ የመድኃኒት አቅርቦት የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ምርት፣ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታ እና ዲጂታል ሄልዝ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሽሪ አኒል ኩማር ራይ ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እየተገበረች እንደምትገኝም ገልጸዋል።
የህንድ ባለሀብቶችም ያለውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለኩባንያዎቹ የኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል ኢንቨስትመንት አማራጭን በተመለከተ ገለጻ እንደተደረገላቸው ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025