አዲስ አበባ፤መጋቢት 28/2017(ኢዜአ):-በተለያዩ አገሮች የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶች ምርትን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ተጨማሪ አቅም እየፈጠሩ መሆኑተገለጸ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፥መንግስት ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
በዚህም ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ ለማስተዋወቅና የገበያ ተደራሽነታቸውን ለማስፋት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩነቶች ላይ የሚደረገው ተሳትፎ መጨመሩን ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ በ2025 በቻይና በተደረገው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የገቢ ምርቶች ፣በጃፓን ኦሳካ የቅባትና እና ጥራጥሬ ትርዔት እንዲሁም በዱባይ የንግድ ትርዔት ላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል።
የንግድ ትርኢቶቹ የኢትዮጵያን ምርት ከማስተዋወቅ በተጨማሪ አዳዲስ ስምምነቶችን በመፈጸም በዘርፉ የሚገኘው ገቢ እንዲያድግ ትልቅ አስተዋጾኦ እያበረከቱ መሆኑን ነው ያስረዱት።
ለአብነትም በዱባይ የንግድ ትርዒት የተሳተፉ 31 ኩባንያዎች በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ኩባንያዎች ተጨማሪ የውል ስምምነት መፈራረማቸውን አንስተዋል፡፡
አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ላኪዎችን በማበረታታት እንዲሁም ቅድሚያ በመስጠት ለውጤታማነት አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠሩን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አስታውቀዋል።
በተለያዩ አገራት የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ እያሳደጉ በመሆኑ እንደ አገር የሚደረገው ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶት ተሳትፎ ካደረጉ የንግድ ድርጅቶች መካከል የማይክሮ ፋርማ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲል ታረቀኝ በበኩላቸው፤ የማይክሮ ፋርማ የግብርና ምርቶችን በመያዝ በዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በንግድ ትሪዒቶቹ ምርቶችን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ ደንበኛን ከመፍጠር አኳያ ትልቅ ሚና መጫወቱን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም እንዲህ ዓይነት ዝግጅቶች የኢትዮጵያን ምርት ይበልጥ ለማስተዋወቅ እና ተጨማሪ የገበያ መዳረሻዎችን ለመፍጠር ወሳኝ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመልክተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025