የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2017 የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደርዕይን ከፈቱ

Apr 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2017 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2017 የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደርዕይን ከፍተዋል።

አውደ ርዕዩ "ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መር ሃሳብ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።

በመርኃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣የአዲስ አበባ ምክርቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በአውደ ርዕዩ ከ200 በላይ የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያቀረቡበት ነው፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ አስተዳደሩ ቀዳሚ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዋነኛው ነው።

የዘርፉን ተግዳሮት በመፍታት ከተማዋን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፥ መንግስት የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረገ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህ ሂደት የአምራች ኢንዱስትሪ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፥ ለአምራቾች መሰረት ልማቶችን በማሟላት፣ የፋይናንስና ማሽነሪ አቅርቦት በማሳደግ እንዲሁም ማስፋፊያ ቦታዎችን በማቅረብ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.