አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2017(ኢዜአ)፦ በናይጄሪያ የመከላከያ መረጃ ዋና ኃላፊ ፓርከር አንዳያዳይ የተመራ ወታደራዊ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ላይም የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ አባላት ስለኢንስቲትዩቱ ስራዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሁሉም” በሚል መሪ ሐሳብ ከሚሠራቸው ሥራዎች በተጨማሪ የአፍሪካ ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም እንዲያቋቁሙ መነሻ መሆን መቻሉን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ ውስጥ በዘርፉ በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖር አኅጉሪቱ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ እንዳትሆን እንቅፋት መሆኑንም ገልጸዋል።
የናይጄሪያ ወታደራዊ ልዑካን ቡድን አባላት በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ከአህጉር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ግዙፍ ዳታ ሴንተር መገንባቱን እንዳደነቁ የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።
የሰው ሃብት ልማት ላይ እየሠራ ያለው ሥራም የሚያኮራ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ለአፍሪካ ሀገራት አርዓያ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025