የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በሀረሪ ክልል በበጋ መስኖ አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ውጤታማ ሆነናል-አርሶ አደሮች

Apr 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦በሀረሪ ክልል የከርሰ ምድር ውሃን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በበጋ መስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ውጤታማ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ።


በክልሉ ከዚህ በፊት ብዙም ያልተለመደ የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም በመስኖ አትክልት በማልማት ጥሩ ገቢ እያገኙ ካሉት አካባቢዎች አንዱ የዲሬጠያራ ወረዳ አንዱ ነው።


የዲሬጠያራ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር በክሪ አብዱራህማን፥ በቃሪያ፣ ጎመንና ሌሎች አትክልቶች በማምረት ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።


በዚህ በመጀመሪያ ዙር የመስኖ ልማት ከጎመን ምርት ሽያጭ ከ57 ሺህ ብር በላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን አሁንም በሁለተኛ ዙር ያለሙትን አትክልት ለሽያጭ እያደረሱ መሆኑን ገልጸዋል።


ባለፈው ዓመት ከቃሪያ ምርት ከ300 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን አስታውሰው፥ በተያዘው ዓመት ከፍ ያለ ገቢ እንደሚያገኙም አንስተዋል።


ሌላው የወረዳው አርሶ አደር ቦና ጀማል በበኩላቸው፥ የሽንኩርት ምርትን በመስኖ በማልማት ጥሩ ውጤት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።


በአካባቢው አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት ውጤታማ እንዳደረጋቸው አንስተው፥ከምርታቸው በሚያገኙት ገቢ ከራሳቸው አልፎ ቤተሰባቸውን እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።


የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ዑመር በበኩላቸው በክልሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በአነስተኛ መስኖ ልማት ስራ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል።


በክልሉ በዚህ ዓመት በመስኖ ልማት 4 ሺህ 700 ሄክታር መሬት መልማቱን ገልጸው፥ይህም የህዝቡን ኑሮ ማሻሻሉን አስታውቀዋል።


የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ አርሶ አደሩ በአሁኑ ወቅት አትክልትና ፍራፍሬ ስራን እያስፋፋ እንደሚኝ ገልጸዋል።


በዚህም በመስኖ ልማት አርሶ አደሩ ከራሱ አልፎ ገበያን በማረጋጋት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።


በቅርቡ በሀረሪ ክልል የልማት ጉብኝት ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ እንደገለጹት፥ በክልሉ ከተረጂነት ወጥቶ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ እየሆነ ነው።


በዚህም በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በምግብ እህል አቅርቦት እራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ርብርብ እንደአገር የተጀመረውን ስራ ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።


እንደ ሀገር በልማት ላይ ጠንክሮ መስራት ከተቻለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተረጂነት ለመላቀቅ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ስራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.