የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል- ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ

Apr 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለጹ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የስምንት ወራት የስራ አፈጻጸም ዛሬ ገምግሟል።

ቋሚ ኮሚቴው በተቋሙ የመስክ ምልከታም አድርጓል።


የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ሚኒስቴሩ በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የፊሲካል እና ታክስ ፖሊሲዎች የመተግበር፣ የዋጋ ንረትን የማረጋጋትና ለመሰረታዊ ግብዓቶች ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ የመደጎም ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የበጀት ጉድለትን በአግባቡ ማስተዳደር እና የእዳ ሽግሽግና እፎይታ ማግኘት መቻሉን አመልክተዋል።

የውጪ ሀብትን ከምንጊዜውም በላይ በማሰባሰብና የሀገር ወስጥ ገቢን በማሳደግ የመንግስትን ፋይናንስ አስተዳደር ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በበኩላቸው የፊሲካል ፖሊሲንና የመንግስት ፋይናንስን ተግባራዊ አስመልክቶ በስምንት ወራቱ የተከናወኑ ስራዎችን አንስተዋል።

የኑሮ ወድነት የሚያድግበትን ፍጥነት የመቀነስ፣ በተለያዩ የታክስ ፖሊሲ ህጎች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር እና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የማገዝ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ጋር በተገናኘም ክፍያዎች በተለይ ለክልሎች በወቅቱ እየተለቀቀ መሆኑንና የኦዲት ግኝቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል።


በ2018 በጀት አመትም የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የዋጋ ንረቱ የሚጨምርበት ፍትነት ይበልጥ እንዲቀንስ ለማድረግ ይሰራል ነው ያሉት።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ ውይይቱንና ምልከታውን ተከትሎ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር አንጻር የፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የመንግስት ንብረት አስተዳደር፣ የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዢ እና በክልሎች የፕሮጀክት አፈጻጸም የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

በኦዲት ግኝት እርምጃ አወሳሰድ እና በሌሎች የፊሲካል ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰባቸውንም የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.