
ሀዋሳ ፤ሚያዚያ 17/2017(ኢዜአ):- በሲዳማ ክልል የቴክኖሎጂ ዘርፉን ለስራ እድል ፈጠራ በማዋል የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
በሲዳማ ክልል የቴክኖሎጂ፣ ክህሎትና የጥናትና ምርምር አውደ ርዕይ በሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ ተከፍቷል።
የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በራሳ፤ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዘርፉን በማጠናከር ልማትን ለማፋጠን ግብ ተቀምጦ እየተተገበረ ነው ብለዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም በክልሉ በመፍጠርና በማሻሻል እንዲሁም መቅዳትና ማሸጋገር የቻሉ በርካታ ተወዳዳሪ ዜጎች መፈጠራቸውን ጠቁመዋል።
ውጤቱንም ይበልጥ ለማሳደግ በዘርፉ ተሰማርተው ለሚንቀሳቀሱ አካላት ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም አቶ በየነ ተናግረዋል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ተወካይና የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ለቴክኒክና ሙያ ዘርፎች በሰጠው ትኩረት ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ይህንንም ለማጠናከር ሙያንና ክህሎት ለማሳደግና ልምድ ለመለዋወጥ የሚያግዙ ውድድሮችና አውደ ራዕዮች እየተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው በክልሉ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ዘርፉ ያለውን ዕምቅ አቅም ለስራ ፈጠራና የዜጎች ህይወት የሚለውጥ እንዲሆን ታቅዶ በመሰራቱ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል።
በተለይም ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ለመቀላቀል የነበረው አመለካከት በመቀየሩ በርካቶች በዚህ ሂደት እያለፉ ህይወታቸውን እየቀየሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በክልሉ ከራሳቸው አልፈው ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ መወከል የቻሉ ሰልጣኞች መፈጠራቸውን አንስተው ''ይህን አጠናክረን መቀጠል ይገባናል'' ብለዋል።
ለአራት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ውድድር በክልሉ ከሚገኙ ከመንግስት፣ከግል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተውጣጡ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች እንዲሁም በኢንተርፕራይዞች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች መቅረባቸውን ገልጸዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026