
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከWebuild Group ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህብራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከWebuild Group ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተገናኝተን እየተሳተፉባቸው ባሉ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
በጥቂት ወራት ውስጥ በሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እንዲሁም በኮይሻ ግድብ ፈጣን አፈፃፀም እንደታየው ሀገራዊ ግቦቻችንን በማሳካት ረገድ ከWebuild Group ጋር ያለን ትብብር ወሳኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በዛሬው ውይይታችን በመሠራት ላይ ባሉት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ በፍጥነት በታገዘ ውጤታማነት ላይ ፈጠራን እና ዘላቂነትን የሥራዎቻችን ማዕከል አድርገን መያዝ እንደሚገባ ተነጋግረናል ብለዋል።
ውይይታችን የኢኮኖሚ እድገትን በመምራት እና የረጅም ጊዜ ልማትን በመደገፍ ሀገር የሚያሻግሩ ፕሮጀክቶችን በመከወን ረገድ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያንፀባረቀ ነበር ሲሉም ገልጸዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026