የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትግበራው አሳታፊና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተፈጥሯል - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

Jun 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትግበራው አሳታፊና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መፈጠሩን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሁለተኛው ምዕራፍ 5ኛ ዙር "ስለ ኢትዮጵያ" የፓናል ውይይት" ስራ ዕድል ፈጠራ ስለ ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡


የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት፤ በበይነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሃብቶች የበለፀገች መሆኗን ተከትሎ ሃብቶቿን ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራች ነው ብለዋል።


በዚህም ያላትን ጸጋ በመጠቀም የክህሎት ልማትን፣ የስራ ዕድል ፈጠራንና የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን በማስተሳሰር አመርቂ ውጤቶችን እያስመዘገበች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡


በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትግበራው አሳታፊና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መፍጠር መቻሉንም ገልጸዋል፡፡


ይህም ዜጎች በሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ለማጎልበት ምቹ ድል እንደሚፈጥርም አክለዋል።


በዚህ ረገድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክህሎት ልማት ላይ ለሚያከናውነው ተግባር ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራው በእጅጉ እያገዘ ስለመሆኑም አንስተዋል።


የስራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ የዜጎች የህልውና ጉዳይ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ እሴት የታከለበት የስራ ዕድል ተደራሽነትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።


ለዚህም በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ የሀገራትን ልምድና ተሞክሮ የቀመረና አዳዲስ የስራ አማራጮችን ተደራሽ ያደረገ የስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።


ይህም በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጎልቶ የሚታይ የስራ ዕድል ተጠቃሚነትን ተደራሽ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ መፈጠሩን ነው የጠቀሱት።


በዘርፉ ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎች ለክህሎት ልማት ስራ ስኬታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልፀው በዚህም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ነው ያሉት።


የተመዘገቡ ውጤቶችን ከዳር ለማድረስ የፋይናንስ ስርዓቱን ተአማኒና ፍትሃዊ ማድረግ ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አንስተዋል።


እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያለውን አቅም አሟጦ በመጠቀም የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ለአካታች ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጉላት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.