ነገሌ ቦረና፣ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፦በጉጂ ዞን በመስኖ ከለማው መሬት ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአትክልትና ስራስር ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በዞኑ ከነሀሴ አጋማሽ እስከ ታህሳስ መጨረሻ የመጀመሪያው ዙር ከየካቲት መጀመሪያ እስከ ግንቦት መጨረሻ 2ኛ ዙር የመስኖ ልማት ወቅት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
የጽህፈት ቤቱ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ መንግስቱ ሂርባዬ፤ በዞኑ በ2ኛው ዙር የመስኖ ስራ 12 ሺህ 78 ሄክታር መሬት መልማቱን ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት በመሰብሰብ ለገበያ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው፥ እስካሁን በተካሄደው ስራም ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአትክልትና ስራስር ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
በመስኖ ከለሙት የአትክልትና ስራስር አይነቶች መካከል ድንች፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ጎመን፣ ቃሪያ፣ ካሮት፣ ቀይ ስርና ሰላጣ የመሳሰሉትን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡
ምርቱን ለማሳደግ 43 ሺህ 91 ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮና 1 ሺህ 626 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ፤16 ሺህ 803 ኩንታል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉን ጠቅሰዋል፡፡
በልማቱ ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን 23 ሺህ 797 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡
የመስኖ ልማቱን ምርታማነት ለማሳደግ ከማሳ ዝግጅት እስከ ምርት አሰባሰብ ባለው ሂደት የባለሙያ እገዛና ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025