አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦የፋይናንስና የግዢ ሕጎች አፈፃፀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በሳይንሳዊ ጥናት ለማስወገድ የተጀመሩ ተግባራትን ማጠናከር ይገባል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ(ዶ/ር) ተናገሩ።
የፍትህ ሚኒስቴር ባጠናው የፌዴራል የፋይናንስና የግዢ ሕጎች የአፈፃፀም ክፍተት መንስኤዎችና ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃዎችን የሚጠቁም የዳሰሳ ጥናት ማዳበሪያ መድረክ ተካሂዷል።
በውይይቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ(ዶ/ር)፣ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ አበራ ታደሰ እና የሚመለከታቸው ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።
የዳሰሳ ጥናቱ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶችን የ2013 እና 2014 በጀት ዓመት የዋና ኦዲተር የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት መስረት አድርጎ የተከናወነ ነው።
ጥናቱ በአራት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ሕግን ያልተከተሉ ወይም የክፍያ መስፈርቶች ሳይሟሉ የሚፈጸም ክፍያ፣ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ በተመለከተ፣ ተከፋይ ሂሳቦች በሚመለከለት እና የግዥ ሂደት አለመከተል ላይ ማተኩሩ ተጠቅሷል።
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ የፍትህ ሚኒስቴር የፌዴራል የፋይናንስና የግዢ ሕጎች የአፈፃፀም ላይ የሚስተዋሉ ጥሰቶችን ለመለየት ያጠናው ጥናት አበረታች ነው።
ጥናቱ በአሰራሮች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት የፋይናንስና የግዢ ሕጎችን በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
በዚህም በባለድርሻ አካላት የተሰጡ ግብዓቶችን በማካተት አሁን ካለበት የበለጠ አዳብሮ ወደ ሥራ ማስገባት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በቀጣይም በነዚህ ዘርፎች የሚስተዋሉ ከፍተቶችን በሳይንሳዊ ጥናት ለማስወገድ የተጀመሩ ተግባራትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ በበኩላቸው ጥናቱ የተደረገው የፋይናንስና የግዢ ሕጎችን መተግበር የመንግስት ሀብት ወይም በጀት ከብክነት እና ከጥፋት ለመከላለከል ነው ብለዋል።
ሕጎችን ባግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የሀብት አሰባሰብና የወጪ አስተዳደርን በአግባቡ በመምራት የመንግስትን የልማት ስራዎች እንዲያግዙ ለማስቻል የተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጥናቱ ከዚህ መድረክ የተገኙ ምክረ ሃሳቦችን በማካተት የበለጠ ዳብሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ገልፀዋል።
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ ጥናቱ በቀጣይ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን ማካተት እንዳለበት ተናግረዋል።
የፌደራል ዋና ኦዲተር ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ አበራ ታደሰ በበኩላቸው ጥናቱ መንስኤዎችን ለመለየትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025