የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ለሥራ ሥምሪት ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎችን በእውቀትና ክህሎት የማብቃቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Jun 23, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ)፦ ለሥራ ሥምሪት ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎች ለሥራው በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ መንግስት ክህሎትን መሰረት ያደረገ የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡

ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ዜጎች ለውድድር የሚያበቃቸውን ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና እንዲወስዱና ሥራ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በርካታ ወጣቶች በአጭርና በረጅም ጊዜ ስልጠና ክህሎታቸውን በማዳበር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ውጤታማ መሆን ችለዋል ብለዋል፡፡

መንግስት ለዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ እድል ከመፍጠር ባለፈ ክብራቸው ተጠብቆ ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን እና አኗኗራቸውን በማስተዋወቅ የሀገራቸው ዲፕሎማት እንዲሆኑ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት በውጭ አገራት የሥራ ሥምሪት የሚያገኙ ዜጎች የሀገራቸውን እሴት ማስተዋወቅ የሚችሉበት ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ ስልጠና እየሰጠ ነው ብለዋል፡፡

ዜጎች ባፈሩት ጥሪትና በቀሰሙት እውቀት ለራሳቸውና ለሀገራቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር መፍጠር የሚችሉበት አሰራር መዘርጋቱን ገልጸዋል፡፡

በዓለም ላይ ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ በ20 ዋና ዋና ዘርፎች ለሥራ ስምሪት የሚያግዝ ስልጣነ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.