የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከኮካ ኮላ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሊዩሳ ኦርቴጋ ጋር ተወያዩ

Jun 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2017(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከኮካ ኮላ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሊዩሳ ኦርቴጋ ጋር በአንጎላ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

ውይይታቸውም ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቱን ማስፋት በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ውይይቱን የተከታተሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኮካ ኮላ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1958 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራውን ማከናወን መጀመሩን ጠቅሰው ከዛ ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል በመፍጠርና ኢኮኖሚውን በመደገፍ ላበረከተው አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል።

ኮካ ኮላ የሚጠበቅበትን ማኅበራዊ ሀላፊነት በመወጣት በኩል እያበረከተ ላለው አስተዋጽዖ አመስግነው አሁንም ኩባንያው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቱን እንዲያሰፋ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር፣ የመሰረተ ልማት መስፋፋትና ሌሎች ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢዎች ኮካ ኮላ ኢንቨስትመንቱን እንዲያጠናክር የሚያስችሉ መሆናቸውን በውይይቱ መነሳቱን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.