የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ከፍተኛ ለውጥ አምጥታለች- የዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት

Jun 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ከፍተኛ እምርታ ማስመዝገቧን የዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት አስታወቀ።


የዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት (ITU) የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ኢማኑኤል ማናሴህ ኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ በመቅረጽ እና በመተግበር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት እያከናወነች ያለውን ስራ የሚደነቅ መሆኑን ከኢዜአ በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።


ዓለም አቀፍ ትስስር እና ዘላቂ የዲጂታል ትራስፎርሜሽን የህብረቱ ስትራቴጂካዊ ግቦች ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቷን አመልክተዋል።


ህብረቱ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ቀረጻ እና ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።


ቀጣናዊ ዳይሬክተሩ የኦንላይን ትስስር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዋንኛ የልብ ትርታ መሆኑን ጠቅሰው ዲጂታላይዜሽንን እውን ለማድረግ የሚያስችል መሰረት ነው ብለዋል።


በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ የዲጂታል አድማስን በማስፋት አስደናቂ ስራ ማከናወኗን ነው የገለጹት።


በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዲጂታል አገልግሎቶች አማካኝነት የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥርን በአጭር ጊዜ ከ50 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ትልቅ ስኬት ነው ሲሉ ተናግረዋል።


የኢትዮጵያን መጻኢ ጊዜ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኔቬሽን ስራዋ ውስጥ እያየን ነው ብለዋል።


የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ ለዲጂታል ልማት በተጨባጭ የሰጠችውን ትኩረት በግልጽ እንደሚያመላክትም ነው ያብራሩት።


ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት እ.አ.አ በ1865 የተቋቋመ አንጋፋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ኤጀንሲ ነው።


ተቀማጭነቱን በስዊዘርላንዳድ ጄኔቫ ያደረገው ህብረቱ ከኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ጋር የተያያዙ ስራዎችን በዋናነት ያከናውናል።


ዓለም አቀፍ ተቋሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ 194 አባል ሀገራት አሉት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.