አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ )በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤ ላይ አገልግሎትን የሚያዘምኑና ተደራሽነትን የሚያሰፉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለአውደ ርዕይ ቀርበዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነነት አስተዳደር የድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መድሃኒት ማድረስና የኬሚካል ርጭት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የፈጠራ ውጤቶችን አቅርቧል።
በአስተዳደሩ የፕሮጀክት ማናጀር ካሳ አጠና ድሮኖቹ ከጤና እና ግብርና ዘርፎች ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚችሉ እንደሆኑ አብራርተዋል።
በጤናው ዘርፍ የጸረ-ወባ ኬሚካል ርጭት፣ መድሃኒትን የማድረስና ሌሎች አገልግሎቶችን በፍጥነት መስጠት የሚችሉ እንደሆኑ አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በግብርናው ዘርፍም የጸረ-አረም ርጭት አገልግሎትን መስጠት የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ፈጣን የጤና አገልግሎትና የህሙማንን ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር የድሮን ቴክኖሎጂ ፈጣን አገልግሎት በማቅረብ አገልግሎትን እንደሚያሳልጥ ነው የተናገሩት።
በአሁኑ ወቅት በተወሰኑ የአገሪቱ አካባቢዎች መድሃኒቶችን በማድረስ አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ገልጸው የግል ባለሃብቶች በዘርፉ ኢንቨስት ቢያድርጉ ለጤናው ዘርፍ አገልግሎት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመዋል።
የአለርት ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ወቅት ሂደቱን ለምርምርና ለማስተማሪያ ቀርጾ የሚያስቀምጥ የቴክኖሎጂ ውጤት አቅርቧል።
የቀዶ ጥገና ክፍል ነርስ ናትናኤል ብርሃኑ ቴክኖሎጂው የቀዶ ጥገና ሂደትን ለምርምር፣ ለማስተማሪያነትና ምክረ ሃሳብን ከባለሙያዎች በቀጥታ ለማግኘት የሚያስችል እንደሆነ አብራርቷል።
ለሆስፒታሎች ወረቀት አልባ አሰራርን በማልማት ያቀረበው ኢ-ቴክ የተሰኘ ተቋም ከፍተኛ የማርኬቲንግ ባለሙያ ደሳለኝ ዋሚ አሰራሩ የታካሚዎችና ህክምና ተቋማትን መረጃ ልውውጥ የሚያሳልጥ እንደሆነ አመላክቷል።
በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን በኢኖቬሽን የሚደግፉ የመንግስት እና የግል ተቋማት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን በአውደ ርዕዩ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025