ጎለ ኦዳ፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት እና በጥራት ገንብቶ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ቸርነት ገለጹ።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎለ ኦዳ ወረዳ ከ176 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ ሁለት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ቸርነት እንዳሉት የክልሉ መንግስት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራን በልዩ ትኩረት እያከናወነ ነው።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም እየተገነቡ የሚገኙት ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድ በበኩላቸው፤ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ህዝቡ ለሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ እየተሰጠ ነው።
በዛሬው እለትም በዞኑ ጎለ ኦዳ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች ከ176 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡት ሁለት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የዚሁ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በዞኑ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ፣ በፍጥነትና በጥራት የማጠናቀቅ ስራም በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በወረዳው ጮጲ ደጋጋ እና ዲማ ሚስራ ቀበሌ የተገነቡ ሁለት የውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ የውሃና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጀማል ሀሰን ናቸው።
ለንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቹ አስፈላጊ የሆኑ የውሃ መስመሮች ዝርጋታ፣ ማከፋፈያ ቦኖዎች፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከሮችና ሶላር የተገነቡላቸው መሆኑን ጠቁመው ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የቀበሌው ነዋሪ አቶ አብዱላሂ ሻፊ በሰጡት አስተያየት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታው ለበርካታ ዓመታት ሲቸገሩበት ለነበረው ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል።
አካባቢው ውሃ ባለመኖሩ ለራሳቸውም ሆነ ለከብቶቻቸው ከርቀት ስፍራ ውሃ በመቅዳት ይጠቀሙ እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ ወይዘሮ መይሙና መሀመድ ናቸው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራር አካላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ታድሟል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025