አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ በኢንዱስትሪ ንግድና በተለያዩ ዘርፎች በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳለ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጠናው የፀጋ ልየታ አሰራር ጋይድላይን እና የስራ ዕድል መፍጠሪያ መስኮች ጥናት ላይ ለዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው መክፈቻ መርሃ ግብር የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፤ ስልጠናው በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የዘርፉ አመራርና ባለሙያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው።
መዲናዋ ትልቅ ጸጋ ያላት እንደመሆኗ መጠን በኢንዱስትሪ፤ በንግድና በተለያዩ ዘርፎች በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል።
መድረኩ በቀጣይ ዓመት በተሻለ እውቀትና መረጃ ላይ በመመሰረት ለወጣቱ ቋሚ የስራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንድሚሆን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር እና የጥናት ቡድኑ መሪ ጆንሴ ባኔ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የጥናቱ ዋና ዓላማ በከተማዋ የስራ ዕድል ዘርፎችን ለመለየት መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን የስራ ዕድል ለመፍጠር በጥናት የታገዙና መረጃን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መከካል አቶ ናሆም ለማ ጥናቱ የስራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንደሚሆን አመልክተዋል።
ጥናቱ በደንብ ከተሰራበት በከተማዋ የስራ ዘርፎችን በመለየት በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር ያስችላል ያሉት ደግሞ ሌላኛው አስተያያት ሰጪ አቶ ኢብራሂም መሀመድ ናቸው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025