አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ(ጃይካ) በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን የልማት ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ የጃይካ ተወካይ ኬንሱኬ ኦሺማ ገለፁ።
ጃይካ ከኢትዮጵያ ጋር ለዘመናት የዘለቀ የልማት ትብብር እንዳለው ለኢዜአ የገለጹት ተወካዩ፥ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በርካታ ለውጦችን እንዳመጡ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።
ጃይካ በግብርናና ገጠር ልማት፣ በመሰረተ ልማት፣ ኢንዱስትሪያላይዜሽንና በትምህርት ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የገበያ ተኮር ግብርና፣ የሩዝ ምርታማነትና የውሃ ዘርፍ ልማትም ጃይካ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ከሚሰራባቸው የትብብር መስኮች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ጃይካ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችና ሌሎች ዘርፎች ላይ በትብብር እየሰራ መሆኑንና እያደረገ ያለውን የልማት ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ለውጥ እያስመዘገቡ መሆኑን መመልከታቸውን ጠቅሰው፥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የልማት ስራዎች የስኬት ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመላ ሀገሪቱ መሰል የልማት ስራዎችን ለማጠናከር እየተሰራ ያለውን ስራ ጃይካ እንደሚደግፍም ተወካዩ አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025