
ሀዋሳ፤ ሰኔ 28/2017 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳድር "የኢንተርፕራይዞች ሚና ለሀገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ የተዘጋጀውን አውደ ርዕይና ባዛር ከፍተዋል።
በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በክልሉ ያሉ አምራች ኢንተርፕራይዞችን አቅም በማጠናከር ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ይሰራል።

ኢንዱስትሪዎቹ በተሰማሩበት ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆኑ የድጋፍና ክትትል ሥራው በትኩረት እንደሚከናወንም አመልክተዋል።
የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የሥራ ዕድል ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ከፍያለሁ ከበደ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ በአውደ ርዕይና ባዛሩ ላይ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከ220 በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች ይሳተፋሉ።
አምራች ኢንዱስትሪዎቹ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
አውደ ርዕይና ባዛሩ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ ልምድ እንዲለዋወጡና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ሚናው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።

የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡበት በመሆኑም በገበያ ዋጋ ማረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አቶ ከፍያለው ተናግረዋል።
በአውደ ርዕይና ባዛሩ መክፈቻ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026