🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2018(ኢዜአ)፦ በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በሊዝ ፋይናንስ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እመቤት መለሰ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሊዝ ፋይናንስ ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ ለኪራይ የሚያቀርበው አገልግሎት ነው።
በዚህም ባንኩ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድንና በሌሎችም ዘርፎች ለተሰማሩ አምራቾች የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት እመቤት መለሰ (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፤ መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በቂ መሰረተ ልማት መገንባቱን አንስተዋል።
ይሁንና መሰረተ ልማታቸው በተሟላ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተወዳዳሪ ባለሃብቶች በሚፈለገው ልክ አለመግባታቸውንም ነው ያነሱት።
ይህን ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያቀርበውን የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በዚህም በተለይ በግብርና ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በሊዝ ፋይናንስ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።
የግብርና ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ማሳደግና የምርት ብክነትን መቀነስ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ በቂ ግብዓት ማቅረብ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።
በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የበለጠ ውጤታማ የሚሆኑበትን የሊዝ ፋይናንሰ አቅርቦት ማሳደግ ላይ ጥናትና ምርምር የማድረግ ተግባር የሁሉም ባንኮች ድርሻ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።
ከዚህ አኳያ ባንኩ በሊዝ ፋይናንስ ያለውን የካበተ ልምድ በመጠቀም ከሌሎች ባንኮች ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025