🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፡- የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በሀገር ውስጥ ለመገንባት መወሰኑና ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ለግብርናው ሴክተር ማርሽ ቀያሪ ተግባር መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው ይታወቃል።
በዚሁ ወቅትም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በዓመት 3 ሚሊየን ቶን ማዳበሪያ አምርቶ ያቀርባል ማለታቸው ይታወሳል።
ይህን አስመልክቶም በግብርና ሚኒስቴር የግብዓት አቅርቦት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ተስፋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ፕሮጀክቱ በሀገራችን የመጀመሪያ በመሆኑ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ዕክሎችን በማረቅ ረገድ የጎላ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

እንደ ሀገር ዘርፈ-ብዙ ጥቅም እንዳለው ጠቁመው፤ በተለይም ለግብርናው ዘርፍ ማርሽ ቀያሪ ትልቅ ተግባር ስለመሆኑ በአጽንኦት ገልጸዋል።
ቀዳሚው የግብርና ዘርፍ ተልዕኮ ምርትና ምርታማነትን መጨመር መሆኑን እና ለዚህ ደግሞ ግብዓት ወሳን መሆኑን አንስተዋል።
ተልዕኳችንን በሚፈለገው ልክ ለማሳካት የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በሀገር ውስጥ መገንባቱ ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል።
የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካው በሀገር ውስጥ መገንባቱ የሚጨምራቸው በጎ ነገሮች እና የሚቀንሳቸው ጫናዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በዚህም መሠረት፤ በምንፈልግበት ጊዜ፣ የምንፈልገውን መጠን እና ዓይነት አፈር ማዳበሪያ ለማግኘት ያስችላል ብለዋል።
ለአብነትም ከዓለም ሀገራት ጋር ተወዳድረን የምንፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ዓይነት ለማግኘት ተቸግረን እናውቃለን ሲሉም አስታውሰዋል።
ከዚህ አኳያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በሀገር ውስጥ መገንባቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በአጽንኦት ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025