የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በወላይታ ዞን በግብር አሰባሰብ ላይ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት መሻሻል እያሳዩ ነው

Oct 17, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ፤ ጥቅምት 6/2018(ኢዜአ)፡- በወላይታ ዞን የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በግብር አሰባሰብ ላይ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት መሻሻል እያሳዩ መሆኑ ተገለጸ።

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ የ2018 ሩብ የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ኪራይ እና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር አሰባሰብ ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።


በመድረኩ ላይ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ፤ በበጀት ዓመቱ ከመደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

በዚህም በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

የገቢ አቅም ልየታና የአሰባሰብ ሂደቱ በቴክኖሎጂ ታግዞ ቀልጣፋ የማድረጉ ተግባር መሻሻል ማምጣቱን ተናግረዋል።

በቀጣይም የገጠር መሬት መጠቀሚያ ኪራይና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር አሰባሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል።



የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ተሰማ(ረዳት ፕሮፌሰር)፤ የዞኑን ሕዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በግብር አሰባሰብ ላይ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት መሻሻል እያሳዩ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በዞኑ ኢኮኖሚው ከሚያመነጨ አቅም መነሻ ያደረገ ገቢ በመሰብሰብ ወጪን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረጉ ጥረቶች ውጤት እያመጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ካለው የገቢ አማራጭ አንጻር ብዙ ሊሰራ ይገባል ብለዋል ።

በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማቃለል የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማዘመን እየተደረገ ያለው ጥረት መጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የዞን፣የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.