የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

አቶ አህመድ ሽዴ ከአለም ባንክ የስትራቴጂክ አጋርነት ኦፕሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሚስ አና ብጄርዴ ጋር ተወያዩ

Oct 23, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ)፦ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ጉዳዮች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስ አና ብጄርዴ ጋር በቅድመ-ልማት ፕሮጀክቶች፣ በመካሄድ ላይ ያሉ የሪፎርም ስራዎች እና አዳዲስ የፋይናንሺንግ ዘዴዎች ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ደረጃ ያለው ውይይት አደርገዋል።

ውይይቱ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2025 ከተካሄደው የአለም ገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ግሩፕ አመታዊ ስበሰባ ጎን ለጎን ነው።

በዚህ ወቅት አቶ አህመድ ሽዴ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ ለማሳደግ ያለውን ከፍተኛ ሚና እውቅና በመስጠት እየተደረገ ለሚገኘው የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ አመስግነዋል።

ባንኩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማዘመን፣ ምርታማነትን በማሳደግ፣ አዳዲስ የእድገት መንገዶችን በመፍጠርና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በማጎልበት የስራ እድል ለመፍጠር እና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ያለውን አስተዋፅዖም አንስተዋል።

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋርነት እና ከፍተኛ ድጋፍ እየተካሄዱ በሚገኙ ዋና ዋና ዘርፎች ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ድጋፍን በማረጋገጥ ላሳየው አጋርነት ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የስራ እድል ፈጠራን፣ ዘላቂ መሠረተ ልማቶችንና የሰው ሃይል ልማትን ለማስቀጠል የባንኩ ቀጣይ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መግለጻቸውም ተመላክቷል።

የአለም ባንክ የስትራቴጂክ አጋርነት ኦፕሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሚስ አና ብጄርዴ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ባካሄደው የሪፎርም አጀንዳ ምክንያት የተገኘውን ውጤት አድንቀዋል።

በሪፎርሙ አማካኝነት የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን፣ ከፍተኛ የወጪ ንግድ መጨመሩን በተለይም በወርቅ፣ የተሻለ የሀገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰብ፣ የፊስካል ማገገምን የሚያጠናክር እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ ምቹ የንግድ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ለማሳያነት አንስተዋል።

ዋና ዋና የሪፎርም ርምጃዎችን በመተግበር ረገድ መንግስት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚያበረታቱም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026