🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የበጀት ዓመት 21 ከተሞች ወደ ስማርት ሲቲ ትግበራ እንዲገቡ የሚያስችሉ አሠራሮች መጠናከራቸውን ከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የአከታተም ጥናትና የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት ዴስክ ኃላፊ አስማማው ምኑዬ ለኢዜአ እንዳሉት፤ አዳማ፣ ባሕርዳርና ሐዋሳ ከተሞች ቀደም ብለው ወደ ስማርት ሲቲ ትግበራ ገብተዋል።
በያዝነው የበጀት ዓመትም 21 ከተሞች ወደ ስማርት ሲቲ ትግበራ እንዲገቡ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የስማርት ሲቲ ግንባታና መመዘኛ ሠነድ ተዘጋጅቶ ለክልሎችና ከተማ አሥተዳደሮች መሰራጨቱን ጠቅሰዋል።
ስማርት ኢኮኖሚ፣ ስማርት አሥተዳደር፣ ስማርት አካባቢ፣ ስማርት ሞቢሊቲ፣ ስማርት ነዋሪና ስማርት አኗኗር የተሰኙ ስድስት የስማርት ሲቲ ምሰሦዎች በስማርት ሲቲ ስትራቴጂው ላይ መቀመጣቸውንም አስረድተዋል።
በእያንዳንዱ ምሰሦ ላይም ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሠራሮች መኖራቸውን ነው ያስረዱት።
ስማርት ሲቲ ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው በ ‘ኦንላይን’ እንዲሁም እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባሉ አሠራሮች በርካታ ተቋማትን በአንድ ስፍራ ማግኘት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከተሞች ጽዱ፣ የእግረኛና ብስክሌት መንገዶች፣ የማረፊያ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ እንዲኖራቸው እንደሚያስችልም ገልጸዋል።
ስማርቲ ሲቲ ተጀምሮ የሚያልቅ ሳይሆን ቴክኖሎጂው ባደገ ቁጥር የሚያድግ ሂደት መሆኑን ገልጸው፤ የአንድ ተቋም ሥራ ስላልሆነ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላትና ሕብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025