🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው ሚና ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለፁ።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገቱ በየዓመቱ እንዲጨምር ማድረጉንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር ማስቻሉን ተናግረዋል።
ንቅናቄው በኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን አቅም ለማሳደግና ኢኮኖሚውን ለማጠናከር የተጀመረ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ ሀብትና የሰው ኃይል በመጠቀም የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ፣ ወደ ውጭ የሚላከውን ምርት መጠን መጨመር ላይ የግንዛቤ ለውጥ ማምጣቱን አስታውቀዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያጋጥሙ የአጭርና የረጅም ጊዜ ችግሮችን በመፍታት የማምረት አቅምን በማጎልበትና ተኪ ምርቶችን የማምረት አቅም ማሳደጉንም ገልፀዋል።
በንቅናቄው የተከናወኑ ሥራዎች አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ በኩል አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በ2014 ዓ.ም ላይ የአምራች ኢንዱስትሪው አመታዊ ዕድገት 4 ነጥብ 8 በመቶ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህ አሃዝ በ2017 በጀት ዓመት ላይ በከፍተኛ ደረጃ በማደግ 10 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ከ12 በመቶ በላይ ያስመዘግባል ተብሎ መተንበዩንም ተናግረዋል።
ንቅናቄው በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እያስመዘገበው ያለው መሻሻል የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማጠናከር የሚያደርገውን አስተዋፅኦ በተግባር እያሳየ ይገኛል ነው ያሉት።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026