🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ በኮሪደር ልማት የተገነቡ የመዝናኛ ስፍራዎችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች የከተማውን ገጽታ የቀየሩና ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገሩ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ከትናንት በስትያ መካሄዱ ይታወሳል።
በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በሀገሪቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ባስገኟቸው ስኬቶችና ትሩፋቶች ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራርያ ሰጥተዋል።
የኮሪደር ልማት ቦታና ጊዜን በተመለከተ አዲስ እሳቤ ያዘለ መሆኑን አንስተው በተለያዩ ከተሞች የተከናወኑ የግንባታ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ግንባታዎቹ ስለምንኖርባቸውና ስለምንጋራቸው ቦታዎች አዲስ እሳቤን ያሰረጹ፣ ከፍተኛ የባህርይ ለውጥ ያመጡ እንዲሁም የወጣቶች የፈጠራ አቅም ጎልቶ እንዲወጣ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል።
በልማቱ እውን የሆኑት የመዝናኛና ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወጣቶችና ጎልማሶች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ በተለይ ደግሞ ወጣቶች በስነ ምግባር እንዲታነጹ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
የልማት ስራዎቹ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያዳብሩና ልጆች ከቤት ወጥተው አካባቢያቸውን እንዲያውቁ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኮሪደር ልማትን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ኢዜአ የህዝብ አስተያቶችን አሰባስቧል፡፡
ከአስተያየት ሰጭዎች መካከል አበበ ተሰማ በመዲናዋ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎች አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ፣ ውብ፣ አረንጓዴና ስማርት ከተማ አድርገዋታል ብለዋል።
በአዲስ መልክ የተገነቡት የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፤ መዝናኛ ስፍራዎች እና ማረፊያ ቦታዎች አይን የሚማርኩ፣ በነጻነት ለመንቀሳቀስና ለመዝናናት የሚመቹ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጭ መምህር ፀጋዬ ኃይሌ፤ የወንዝ ዳር ልማቶቹና የመዝናኛ ስፍራዎቹ የከተማውን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገሩ ዘመን የማይሽራቸውና በአርአያነት የሚጠቀሱ ስራዎች ናቸው ብለዋል።
አቶ ዘካሪያስ ታደሰ እንደገለጹት በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ለመዝናኛ ምቹ በመሆናቸው ዘወትር በእግራቸው እየተጓዙ ራሳቸውን እንደሚያዝናኑ ተናግረዋል፡፡
በመዝናኛ ቦታዎቹ ያገኘናቸው ወጣት ጥላሁን መርከበ እና አውላቸው ሲሳይ መሰረተ ልማቶቹ ፅዱና ውብ በመሆናቸው ድካማቸውን ለማቃለል፣ ራሳቸውን ለማዝናናትና ለማደስ ምርጫቸው እንደሆኑ አስታውቀዋል።
መሰል የመዝናኛ ስፍራዎች ወጣቶች ጊዜያቸውን ባልተገባ ቦታ እንዳያጠፉና ላልተፈለገ ወጪ እንዳይዳርጉ ያግዛሉ ነው ያሉት፡፡
የኮሪደር ልማቱ አካል የሆነው የወንዝ ዳር ፕሮጀክት በወንዞች ላይ የሚከሰተውን ለጤና ጠንቅ የሆነ መጥፎ ሽታና ብክለት አክሞ ንጹህና ሳቢ እንዳደረጋቸውም ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025