የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በሀገር ደረጃ የተወጠኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ዕድገት የሚያፋጥኑ ናቸው

Nov 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፤ ጥቅምት 23/2018 (ኢዜአ):-በሀገር ደረጃ የተወጠኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማፋጠን ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግሩ መሆናቸውን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህርና ተመራማሪ ዘሪሁን ተምሳስ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉባ ላይ ይፋ የተደረጉት ፕሮጀክቶች የሀገሪቷን የኢኮኖሚ መሠረቶች ወደ ብዝሃ ዘርፍ በማምጣት የተጀመረውን ሀገራዊ የብልፅግና ጉዞ በአስተማማኝ መንገድ ለማስቀጠል እንደሚያስችሉ ተመልክቷል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህርና ተመራማሪ ዘሪሁን ተምሳስ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ መንግስት የወጠናቸው የልማት ስራዎች የሀገርን ከፍታ የሚያረጋግጡ ናቸው።

ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር በጀት የሚፈጁት እነዚሁ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በየትኛውም የሀገራችን ዘመን ያልተሞከሩና የሀገርን የለውጥና የዕድገት ጉዞ በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለማዋቀር የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ምሁሩ እንዳወሱት፤ በቢሾፍቱ የሚገነባው ግዙፉ የአውሮፕላን ማረፊያ፣የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኒውክለር ማበልፀጊያ ፕላንት፣ የነዳጅ ማጣሪያና የጋዝ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎችም ፕሮጀክቶች የሀገርን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ይበልጥ በማሳለጥ የዜጎችን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ናቸው።

በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት እና በማስገኘት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለዋጋ ንረት መፍትሄ እንደሚያመጡ ነው ያመለከቱት።

ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ለመሸጋገር የጀመረችውን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ መሰረት እንደሚጥሉም ተናግረዋል።

ይህም ኢኮኖሚን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ አክለዋል ።

እንደ ምሁሩ ማብራሪያ፤መንግስት በሀገሪቱ ታሪክ ግዙፍና አሻጋሪ ፕሮጀክቶች መጀመሩ የአሁንና የቀጣዩ ትውልድ ታላቅ ብስራትና ኩራት ነው።

በመሆኑም እነዚህ አሻጋሪ ፕሮጀክቶች የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኙ ዜጎች እና ምሁራን ልክ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁሉ ርብርባቸውን እንዲያጠናክሩ መልእክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026