🔇Unmute
ጅግጅጋ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፡-ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ የምርምር ማዕከል በመሆን የትውልድና ሀገር ግንባታን የሚደግፉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።
በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዲ አህመድ ሀሰን (ዶ/ር)፤ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእውቀት እና የምርምር ማዕከል በመሆን ለትውልድና ሀገር ግንባታ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ የክልሉን ብሎም የሀገርን እድገት መደገፍ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም በግብርና፣ ስነ- ህይወት፣ ምህንድስና፣ ፊዚክስ እና ሌሎችም ላይ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማሳተም የእውቀትና የምርምር ማዕከል የመሆን ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል።
በማሕበረሰብ አገልግሎቱ በተለይም የትምህርት፣የጤና እና የሕግ አገልግሎቶች እንዲሁም የአቅም ግንባታ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አንስተው፤ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
አሁን ላይ በጅግጅጋ እና በሼኽ ሀሰን የበሬ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ካምፓሶቹ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኘ ያነሱት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ ሶስተኛውን ካምፓሱን በጎዴ ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025