የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ከማዕከሉ የምናገኛቸው የሰብል ዝርያዎች ድርቅና ተባይን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጡ ናቸው-የባምባሲ ወረዳ አርሶ አደሮች 

Nov 10, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ከአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የሚያገኟቸውየሰብል ዝርያዎች ድርቅና ተባይን በመቋቋም የተሻለ ምርት እንደሚሰጡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባምባሲ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

ማዕከሉ በምርምር አውጥቶ በአርሶ አደሮች ማሳ ለማስተዋወቅ ያለማው "BH-520" (ናዳ) የተሰኘ የበቆሎ ዝርያ በአርሶ አደሮችና በግብርና ባለሙያዎች ተጎብኝቷል።


በመስክ ምልከታው ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት፤ የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በየጊዜው የሚያመጣቸው የሰብል ዝርያዎች ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።


ከአርሶ አደሮቹ መካከል በባምባሲ ወረዳ መንደር 47 ቀበሌ ነዋሪ አርሶአደር ሀይሉ በየነ እና የሺብር ዘገዬ በቀበሌያቸው እየለማ የሚገኘው አዲስ የበቆሎ ዝርያ ዝናብ እና ተባይን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።


ማዕከሉ አርሶ አደሩ ምርታማ እንዲሆን በየጊዜው ከሚያፈልቃቸው ምርጥ ዘሮች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን አስታውሰዋል።

የአሁኑ የመስክ ጉብኝትም ማዕከሉ ምርታማነታቸውን በመጨመር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰራ ላለው ስራ ልምድ ለመቅሰም እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

በመስክ ምልከታቸው ያዩት የበቆሎ ዝርያ በጥሩ ቁመና ላይ መገኘቱ የተሻለ ዝርያ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑንም ተናግረዋል።

አርሶ አደር መሳይ አበባው በበኩላቸው፤ የምርምር ማዕከሉ በትንሽ ማሳ ላይ ብዙ ምርት መስጠት የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችን በማፍለቅ ማስተዋወቁን ጠቁመዋል።


ከዚህ በፊትም ማዕከሉ ያወጣቸውን አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በመጠቀም በግብርና ሥራቸው ላይ ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን አክለዋል።

በአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የግብርና ኤክስቴንሽን ተመራማሪና የዘርፉ አስተባባሪ ፍቃዱ ቤኛ ማዕከሉ ለአካባቢው ስነምህዳር ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ የምርምር ስራዎችን በማፍለቅ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።


ከበቆሎ በተጨማሪ በሰሊጥ፣ ቦለቄ እና ማሽላ ላይ በስፋት የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ የምርምር ውጤቱን በማስፋት አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ ነው ብለዋል።

በወረዳው መንደር 48 ቀበሌ በምርምር ያወጣውና በሄክታር 95 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችል "BH-520" (ናዳ) ዝርያም የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል።

የምርምር ማዕከሉ የሚያወጣቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የዘር ብዜት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ፍቅሩ አቡን ናቸው።


አርሶ አደሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ተጠቅሞ በኩታ ገጠም እርሻ ልማት ውጤታማ የግብርና ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ረቂቅ አዋጁ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...

Apr 23, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ በኢኮኖሚው መስክ ትብብራቸውን ያጠናክራሉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...

Apr 17, 2026

በጀጎል ግንብ ውስጥ የሚገነባው የ”ዳር ሀረር” የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...

Apr 12, 2026

በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ማረጋገጥ የሚያስችል የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ማረጋገጥ የሚያስችል ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባ...

Mar 31, 2026