የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አስተዳደሩ ያገኘው እውቅና የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያከናውናቸውን ተግባራት ያጠናክራል

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሕዳር 2/2018 (ኢዜአ)፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጠው የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬሽን እውቅና የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማጠናከር እንደሚያስችለው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬሽን እውቅና አግኝቷል።


አስተዳደሩ ያገኝው የISO 9001:2015 QMS የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬሽን አለማቀፍ እውቅና መሆኑም ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ተቋማት በተሰማሩበት መስክ አስፈላጊ የሆኑ ደረጃዎችን በማሟላት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጠው እውቅናም የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንዲቀጥል ያግዘዋል ነው ያሉት።

ተቋሙም አገሪቱን ከማንኛውም የሳይበር ጥቃቶች ለመከላከል እያከናወናቸው ያለውን ተግባር ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠል ሃገራዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም አመልክተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድ በበኩላቸው፤ የሳይበር ደህንነት በየጊዜው ተለዋዋጭ በመሆኑ ዘመኑን የሚመጥን ዝግጅቶች በማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።


ተቋሙ በዘርፉ ጥራት ያለው አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸው፤ ይሕንን በማስቀጠልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የተቋሙን አሰራሮችን የማዘመን እና የደምበኞችን እርካታ ለማምጣት ቀጣይነት ያለው ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር መዓዛ አበራ (ኢ/ር) በበኩላቸው፥ ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ መስፈርቶችን ማሟላታቸው ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ያስችላል ብለዋል።


ድርጅቱ አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ላሟሉ ተቋማት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸውን ደረጃዎች በመስጠት ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

አስተዳደሩ ያገኘው እውቅና በአገርም ሆነ በተቋማት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችና ጉዳቶችን ለመከላከል እየሰራ ያለውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያስችለው ጠቅሰዋል።


የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር መሠረት በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የጥራት መስፈርት ማሟላት መቻሉ ኢትዮጵያ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያግዛታል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.