የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የከተሞች ፎረም ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ተከናውኖ በስኬት ተጠናቀቀ

Nov 20, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ተከናውኖ በስኬት መጠናቀቁን የአፋር ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

የአፋር ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ መሀመድ አሊ 10ኛው የከተሞች ፎረም መጠናቀቅን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ፎረሙ የአፋር ክልል እንግዳ ተቀባይነቱን በተግባር ያሳየበት እንደነበር ጠቁመው፤ በፎረሙ ለመታደም የመጡ እንግዶችን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ መቻሉን አመላክተዋል።

በፎረሙ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልል የመጡ ከተሞች ስራዎቻቸውን እንዳቀረቡ ገልጸው፤ ተሞክሮቻቸውን በስፋት ማጋራት መቻላቸውን አስታውቀዋል።

ፎረሙ ከተሞች ያሉበትን የእድገት ደረጃ ያሳዩበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ፎረሙ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ተከናውኖ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ልማት ስራዎች በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መጎብኘታቸውን አንስተዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው ከተሞች እድገትንና ብልጽግናን እንዲያረጋግጡ በጋራ ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.