🔇Unmute
ቦንጋ፤ ህዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ያለውን ጸጋ ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋል አመራሩ ከተለመደ አሰራር መውጣትና የአስተሳሰብ አንድነት ማጠናከር እንዳለበት የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ፍቅሬ አማን ገለጹ።
"በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተዘጋጀ ሁለተኛ ዙር ስልጠና ዛሬ በቦንጋ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የክልሉ ዋና መንግስት ተጠሪ ፍቅሬ አማን በዚህ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ ያለውን የልማት አቅም ለመጠቀም አመራሩ የተለመደውን አሰራር መቀየርና የአስተሳሰብ አንድነትን መፍጠር አለበት፡፡

የክልሉ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነውን የግብርና ዘርፍ በማዘመንና ውጤታማነቱን በማሳደግ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ግብዓት እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበትም ነው ያሉት፡፡
በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን ማሳደግ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ከጂኦ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ጋር በቀጥታ እንደሚገናኝም አንስተዋል።
ከአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው ቱሪዝም ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት እመርታዊ ለውጦችን ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመው በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ሃብቶችን በማልማት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

የከተማ ልማትን ጨምሮ ዋነኛ ሀገራዊና ክልላዊ የልማት መስኮችን ለማሳካት አመራሩ የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠርና ተቀራርቦ መስራትን እንዲያጠናክር ማስገንዘብ የስልጠናው አንዱ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
አብሮነትና የውስጠ ፓርቲ አንድነትን ማጠናከር እንዲሁም ተግባራትን በውጤታማነትና በቅንጅት መፈጸም ሌላኛው የስልጠናው ትኩረት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025