🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ግብርናን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ትብብሮችን ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ ተወያዩ።
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ከሩሲያ የግብርና ምክትል ሚኒስትር አንድሬይ ራዚን እና ልዑካቸው ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ኢትዮጵያና ሩሲያ በተለያዩ ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

ግብርና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋነኛው ዘርፍ መሆኑንና ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በምታደርገው ርብርብ ከሩሲያ ጋር ልምዶችን በመለዋወጥ በትብብር መስራት በምትችልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
ውይይታቸውም በሁለቱ መስሪያ ቤቶች መካከል ከፍተኛ ልምድ ልውውጥና የቴክኒክ ትብብርን ያማከለ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግና የሁለትዮሽ ስምምነትም ለመፈራረም መስማማታቸው በውይይቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡
በተለይም በምርጥ ዘር በኩል በጋራ ለመስራት ማቀዳቸው በውይይቱ የተነሳ ሲሆን ለዘይት ጭማቂ ግብዓት በሆነው በሱፍ አበባ ዙሪያ በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ በምግብ ዘይት ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ነው የተባለው፡፡

በሌላ መልኩም ሁለቱ ሀገራት በግብርና ምርምርና ሳይንስ በግሉ ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ስምምነት እንደሚደረግም በውይይቱ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡በግብርና ምርምር ዘርፍ የትምህርት ዕድሎችን ለማመቻቸትም እንዲሁ፡፡
በመጨረሻም ሩሲያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሄደችበትን ርቀት ልምድ ለኢትዮጵያ እንደምታካፍልም ተስማምተዋል፡፡
በሩሲያ ፌደሬሽን አዘጋጅነት የአፍሪካ ሀገራትን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ትናንት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል።

መድረኩ ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ ዘላቂ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ሥርዓትን ለማሳደግ እና የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ሉዓላዊነታቸውን በራሳቸው አቅም እንዲያሳኩ የማስቻል ዓላማ ያለው መሆኑንም ተገልጿል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025