የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እኩል መሮጥ አለብን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Dec 2, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን ብልጽግና ኅልውና ለማረጋገጥ ሁላችንም በየዘርፋችን እኩል መሮጥ ይጠበቅብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል።

በዚሁ ወቅትም፤ አንድ ሀገር ከሌሎች ኋላ ቀረ የሚባለው በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂ መስፈሪያዎች ከፍ ካለው ሀገር ዝቅ ብሎ ሲገኝ ነው ብለዋል።

የእድገት መገታት፣ቀጣይነት ያለው እድገት አለመኖር፣ የፍጥነት መጓተት፣የፖለቲካ አዙሪት፣ የኢኮኖሚ ስብራት የኋላ ቀርነት መገለጫዎች ተደርገው እንደሚወሰዱም አብራርተዋል።

ተቋማዊ ውድቀት፣ ባህላዊ ዝቅጠት እና ኢኮኖሚያዊ ልሽቀት የኋላ ቀርነት መንስኤዎች መሆናቸውንም አንስተዋል።


በጊዜና በዘመን መቀደም የሚያስከትለው ጣጣ መዘጋት፣ መዘግየት እና መንሸራተት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።

እየዘገየን በዘመን ስንቀደም ብዙ ጉዳዮች በእኛ እየተዘጉ ዘመን ሲለወጥ እኛ እዛው ቆመን እንቀራለን ብለዋል።

ስለዚህ አካላዊ አጥር፣ ተቋማዊ (ሥርዓታዊ) አጥር እና ባህላዊ አጥር የተሰኙ ሦስት የሀገር እድገት ከልካይ አጥሮች ካልፈረሱ በስተቀር እንደ ሀገር፣ እንደ ክልል ብሎም እንደ ከተማ እድገት አይመጣም ሲሉ ጠቁመዋል።

ዕውቀትን አጥረን፣ገንዘብን አጥረን እና ማደግ ፈልገን እንዴት ይሆናል? አብረው መሄድ አይችሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እድገት የሚመጣው ዕውቀትና ገንዘብ ያለበትን ቦታ አነፍንፈን ስንስብ እንጅ ስንገፋ አይደለም ብለዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያን ብልጽግና ኅልውና ማረጋገጥ የምንፈልግ ከሆነ የኢትዮጵያን ብልጽግና መሥራት ብሎም መሠረት መጣል ከፈለግን ሁላችንም እኩል መሮጥ ይኖርብናል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026